በሀገራችን በፌደራል ደረጃ የተመዘገቡ ከ3000 በላይ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የሚገኙ ሲሆን በክልሎች ደግሞ ቁጥራቸው በመቶዎች እንደሆነ ይገመታል፡፡ ተቌማቱ በየጊዜዉ በሚያጋጥሟስምቸው ችግሮች ዙሪያ በመወያየት የጋራ ድምፅ በመፍጠር ከመንግስትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት በመወያየት ለኢትዮጵያ እድገት እና ብልፅግና የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ብሎም ጠንካራ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ለመፍጠር የሚያስችል የጋራ መድረክ ለመመስረትና የነበረውን መዋቅራዊ ክፍተት ለመሙላት በማሰብ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ በሰጠው ልዩ ፍቃድ መሰረት የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት መድረክ በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም ሊመሰረት ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት መድረክ በሀገራችን በሚገኙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ስምየኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚንስተር ሆነዉ በመሾምዎ የተሰማንን ልባዊ ደስታ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
ከዚሁ ጋር በማያያዝም ድርጅታችን ከዚህ በፊት ከቀድሞ ጠቅላይ ሚንስተር ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር የጀመረውን የሥራ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ እንደሚሸጋገር ተሰፋ እያደረግን አዲሱ የሥራ ዘመንዎ በስኬት እና በውጤት የታጀበ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን፡፡