በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ 621/2001 ማሻሻያ ሰነድ ላይ ከሙያ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

ዛሬ በአዜማን ሆቴል ለግማሽ ቀን በተደረገው የምክክር ውይይት ላይ ከተለያዩ የሙያ ማህበራት የተወከሉ አባላት የተሳተፉ ሲሆን በ2001 ዓ.ም የወጣዉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ 621/2001 በስራ ላይ ከዋለ ጀምሮ ያጋጠሙ ችግሮችን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ በማቅረብ ከዚህ አልፎም የመፍትሄ ሃሳብ በመጠቆም 47 ገጽ የማሻሻያ ሰነድ ለመንግሥት መቅረቡንና ጉዳዩም በሚመለከተው ክፍል እየታየ ስለመሆኑ፡ የሙያ ማህበራት በልማትና ዴሞክራሲ ስርዐት ግንባታ ያላቸዉን ሰፊ ሚና አስመልክቶም በተግባር የታዩ ልምዶችን በመዳሰስ ዉይይቱ ታኪሂዷል፤በተጨማሪም ለማህበራቱ በህጉ ዘንድ ያሉ ክፍተቶችን በማሳየት በቀጣይ ለሚደረጉ ውይይቶች የጋራ ግንዛቤን ለመያዝ ይረዳ ዘንድ የዚህ ምክክር መድረክ አስፈላጊነት ከፍ ያለ መሆኑ ተብራርቷል፤በወቅቱ ለተደረገዉ ዉይይት የማሻሻያ ህጉን የተወሰኑ ክፍሎች በመምረጥ ሀሳብ ያቀረቡት የህግ ባለሙያው አቶ ወንጌል አባተ ሲሆኑከዚህ በተጨማሪም የምክክሩ አዘጋጅ የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት መድረክ አመሰራረት እና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ አቶ በላይነህ ደስዬ የመድረኩ ፕሮግራም ኦፊስር እንዲሁም የሙያ ማህበራት የጋራ መድረክ እና የዘርፉ ሙያ ማህበራት ጥምረት የመመስረት አስፈላጊነት ላይ አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉ ከኢትዮጵያ የፊልም ሰሪዎች ማህበር ለውይይት የሚሆኑ የመነሻ ሀሳቦች ቀርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ዉይይት ተደርጓል::

Share it now!